#በሊቨርፑል_በኩል
✅ #ሳድዮ_ማኔ እና #ቲያጎ_አልካንትራ ከኮሮና ቫይረስ አገግመው ልምምድ መስራታቸው ለሊቨርፑል በጣም ጥሩ ዜና ነው። በቀጣይ ጨዋታም እንደሚሰለፉ ይጠበቃል። ያገኘነው እድል እንድንጠቀም እና የመሀል ሜዳ የፈጠራ ብቃት እንዲጨምርልን የሁለቱም ተጨዋቾች መመለስ ይሄንን ችግር ይቀርፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
✅ በሌላ በኩል #ጆዋል_ማቲፕ ከጉዳት አገግሞ ልምምድ መስራቱም የኋላ መስመራችን ለመጠናከር ሊሰለፍ እንደሚችል እየተገለፀ ይገኛል። ነገር ግን አዲሱ ፈራሚያችን #ኮስታስ_ቲስሚካስ ከጉዳት እንዳላገገመ እና የነገ ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።
✅ የሊቨርፑል ራስ ምታት ሊሆን የሚችለው #የአሊሰን_ቤከር መጎዳት ነው። የአሊሰን አለመኖር ለሊቨርፑል በግብ ጠባቂ ሰፊ ክፍተት ሊፈጠር ይችላል። ምናልባት አድሪያን ያለውን የብቃት ችግር እና ተደጋጋሚ ስህተት የርገን ክሎፕ ሌላ ግብ ጠባቂ ማለት ኮሚሂን ኬሌሀርን ሊጠቀም ይችላል።
✅ #አሌክስ_ኦክስልድ_ቻምበርሊን አሁንም በጉዳት ምክንያት ጨዋታ ያመልጠዋል።
✅ #መሐመድ_ሳላህ 17ኛ የሊቨርፑል መቶ ጎል ያስቆጠረ ሊሆን ይችላል። እስካሁን በ 158 ጨዋታዎች ብቻ 99 ግቦች በማስቆጠር #ከሮጀር_ሀንት እና #ጃክ_ፓርኪንሰን ቀጥሎ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ፡፡
@ynwa_liverpool_lfc