ክሎፕ አዳማ ትራዎሬን ማስፈረም ይፈልጋል
ከወደ ስፔን እየወጡ ያሉ ዘገባዎች እንደሚያሳዮት ከሆነ ክሎፕ አዳማ ትራዎሬን የማሰፈረም ፍላጎት አለው።
Mundo Deportivoን ጠቅሶ the Express እንደዘገበው ክሎፕ የክንፍ ተጨዋቹን ወደ አንፊልድ ማምጣት ይፈልጋል እና ቀዮቹ ከዎልቭስ ጋር ስምምነት ለማድረግ በቀጣይ ዝውውር በድጋሚ ሲከፈት በይፋ ጥያቄ የሚያቀርቡ ይሆናል።
ዎልቭስ ለ24 አመቱ ኮከብ ዝውውር £63m ዋጋ ይፈልጋሉ ሲል ዘግባው አክሏል።
ሊቨርፑል በክረምቱ ዝውውር ለረዥም ጊዜ ከስፔኑ ኢንተርናሽናል ጋር ስማቸው ተያይዞ ሲነሳ ነበር, ግን ባለፈው ወር የቡድን አጋሩን ዲዬጎ ጆታ አስፈርመዋል።
"SHARE" @YNWA_Liverpool_LFC