#መርሲሳይድ_ደርቢ_መዳረሻ_እውነታ_#2
⚽ ተወዳጁ አሰልጣኝ #ቢል_ሻንክሊ ፣ አደም ላላና ፣ ማይክል ኦዌን ፣ ጄሚ ካራገር ፣ ሮቢ ፎውለር ፣ ስቲቭ ማክማናማን እና ኢያን ረሽ ምን እንደሚያመሳስላቸው ታውቃላችሁ?.......... ከሊቨርፑል ጋር የገነኑ ግን የኤቨርተን ደጋፊ ነበሩ
🏟 ሊቨርፑሎች አስገራሚ ድባብ የፈጠሩበት አንፊልድም መጀመሪያ የኤቨርተን ሜዳ ነበር። ሰማያዊዎቹ አንፊልድን ጥለው ነው ጉዲሰን ፓርክ የሄዱት የሚገርመው በሁለቱ ሜዳዎች መሀከል ያለው ርቀት አንድ ኪሎ ሜትር እንኳን አይሞላም (983 ሜትር)
🔵 በሁለቱ ሜዳዎች መሐል ላይ የሚታየው ሰፊ ሜዳ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ 150 አመት ያስቆጠረው Stanley Park ነው። ሊቨርፑል እዚህ ቦታ ላይ አዲስ ስታድየም ለመገንባት ጥያቄ አቅርቦ ነበር ግን ብልጦቹ አሜሪካውያን ባለሀብቶች መጡና አንፊልድን ለማስፋፋት ወስነው ዕቅዱን ውድቅ አደረጉት።
📌 እናም አንፊልድም ሳይቀየር የሊቨርፑል ዳግማ ትንሳኤ በክሎፕ አገዛዝ ብቅ አለ
👕 ኤቨርተን 🆚 ሊቨርፑል
📆 ቅዳሜ ጥቅምት 07-2013
⏰ ከቀኑ 08:30
🏟 በጉዲሰን ፓርክ
@ynwa_liverpool_lfc